መምህር ታሪኩ አበራ/Emmanuel International Gospel Ministry Based On Eotc

About መምህር ታሪኩ አበራ/Emmanuel International Gospel Ministry Based On Eotc

ዓላማችን ኦርቶዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት ለሕዝብ በማቅረብ ሰዎችን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ማሻገር ነው። /we deliver the truth of the Gospel for all Nations /

Reviews

User

**አሳፋሪው ፍጻሜ***
**ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ መነሳት ፍጻሜው የቁም ሞት ነው።**
መ/ር ታሪኩ አበራ...
Continue Reading

User

**ይህንን ቪዲዮ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይመልከተው**
**ኦርቶዶክሳውያን፣ፕሮቴ ስታንት፣ሙስሊሞች ሁላችሁም በጣም ተጠንቀቁ!!**
ሐሰተኛ ነቢያት የሰይጣን ማሕበር አባላት ናቸው።መጨረሻ ግባቸው ትውልድ እግዚአብሔርን ማምለክ እንዲያቆም ማድረግ ነው።
... ይህ ቪዲዮ ለሰው ሁሉ እንዲደርስ ሼር በማድረግ ወገናዊ ኃላፊነቶን ይወጡ።
ይህንን ፔጅ ላይክ ያድርጉ ትምህርቶችና ዝማሬዎች በፍጥነት ይደርሶታል።
See More

User

***ኢትዮጵያ ሀገሬ እግዚአብሔር ትንሳኤሽን በልጆችሽ ያድርገው**
**በ14 ዓመት ዕድሜው አውሮፕላን ሰርቶ ማብረር የቻለ ባለ ብሩህ አዕምሮ ኢትዮጵያዊ ።**
ወጣቶች እባካችሁ ጊዜያችንና አዕምሯችንን እንጠቀምበት።እግዚአብ� �ር አድሎአዊ አምላክ አይደለም ፍትሐዊ ነው።በልግስና አምላክ የሰጠንና እምቅ ኃያል በደንብ ከተጠቀምንበት ዓለምን የሚያስደምም ድንቅ የፈጠራ ታሪክ ሰርተን የሀገራችንን የድህነት ታሪክና የራሳችንንም ሕይወት በሚደንቅ ሁኔታ እንለውጣለን።
... ሰይጣን አዕምሯችንን በዘረኝነት፣ልባችንን በምቀኝነት ሸምቅቆ እርስ በርስ እያባላ እምቅ ኃይላችንን ሳንጠቀም በድህነት ተቀፍድደን እንድንሰቃይ እያደረገን ነው።የዓለም መሪ የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በሱስ የደነዘዘ፣በመጠጥ የተሽመደመደ፣በአደንዛ� � ዕፅ የፈዘዘ ትውልድ እየበዛባት ነው።እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውስልን።
See More

User

***አርባ አራቱ ታቦት የሚለው ታሪክ መነሻው ምንድን ነው ?***
**በሙሴ ዘመን የነበረው ታቦት አንድ ነው፤ አሁን ለምን በዛ?**
ጎንደር በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ከአክሱምና ላሊበላ ቀጥሎ ታላቋ የመንግሥት ማዕከል ነበረች፡፡ በመንግሥት ማዕከልነት የተቆረቆረችው በአፄ ፋሲል (1624-1660 ዓ.ም) ነው፡፡ ጎንደር የመንግሥት ማዕከል ብቻ ሳትሆን በጊዜው የመንፈሳዊ ትምህርት ማዕከልም ነበረች፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመጻሕፍት ትርጓሜና የአቋቋም ትምህርት/ዜማ/ ይበልጥ የተስፋፋውና በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት በመናገሻ ከተማዋ ጎንደር በነገሥታቱ አማካይነት በመሰባሰባቸው ሲሆን ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ መንፈሳዊ ትምህርት በስፋት የሚሰጥባት የትምህርት ማዕከል ለመሆን ችላለች፡፡
...Continue Reading

User

**በዚህ ሰው ላይ ግፍ የፈጸማችሁ ባለ ሥልጣናት በእግዚአብሔር ፊት ወድቃችሁ ንስሐ ግቡ። ለ 25 ዓመት አንድን ታላቅ ፕሮፌሰር ከዩኒቨርስቲ በግፍ አውጥታችሁ ገበሬ ማድረጋችሁ አንድ ሰው ሳይሆን ያንገላታችሁት አንድ ትውልድ ነው የገደላችሁት።**
ብዙ የውጭ ዜጎች በጻፋቸው በርካታ የምርምር መጻሕፍቱ ሲጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ግን ይህንን ሰው እንዳይጠቀሙበት አፍኖ ማሰቃየት እግዚአብሔር ለምድራችን የሰጠንን ስጦታ ነጥቆ የመቅበር ያህል ነው።በትውልድ ላይ ጥላቻና ግፍን የፈጸማችሁ ሰዎች የመዳን ቀን ዛሬ ነው።ፈጥናችሁ ንስሐ ግቡ አሊያ ግን ጌታ መቅረዛችሁን ከፊታችሁ ይወስዳል።ፓይለቱ በግፍ ተባሮ ገበሬ ሲሆን፣ፕሮፌሰሩ በግፍ ተገፍቶ ገበሬ ሲሆን፣የሰው ደም በግፍ ሲፈስ ሌላም ያላየነው ግፍ በምድራችን ሲበዛ የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ከሰገባው ይመዘዛል። አመጸኞችንም በታላቅ ቁጣ ይቀጣል።

User

"የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም። "ኤር 3፥16
#ማሳሰቢያ ይህንን ጽሑፍ ሼር በማድረግ ቢያንስ አንድ ሰው ይመልሱ።
መ/ ር ታሪኩ አበራ
...Continue Reading

User

**ዮርዳኖስ**
**The River of Jordan**
ለሌሎችም ሼር ያድርጉት።

User

**ታላቁ ተአምር** እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ ከተአምራት ሁሉ የሚልቀው ታላቅ ተአምር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ለማዳን ሰው የሆነበት ጥበብ እጅግ ይልቃል።**ታላቁ ተአምር** እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ ከተአምራት ሁሉ የሚልቀው ታላቅ ተአምር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ለማዳን ሰው የሆነበት ጥበብ እጅግ ይልቃል።

User

***ቃና ዘገሊላ***
**ድንግል ማርያም የሰዎች ጉድለት ያሳዝናታል፣ ሰዎች የማይረዱንን የውስጥ ገመናችን እሷ ይገባታል፣ችግርና ስደትን በሕይወቷ አሳልፋለችና ለተቸገረ የሚራራ ርኅሩህ የሆነ የክርስቶስ ልብ አላት።ለተጨነቁም የሚድረስ ትልቅ ስብዕና አላት፣ ጉድለታችንም እንዲሞላ ኤልሻዳይ የሆነ ልጇን ትማልዳለች፤ ክርስቶስ ደግሞ በጉድለታችን ውስጥ ክብሩን ይገልጣል፤ክብር ለስሙ ይሁን።**
በማስተዋል ላነበበው መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን እውነታ በግልጽ አስቀምጦታል።የሰዎች ችግር እንዲወገድ ልጇን ጠየቀች ልመናዋም መልስ አገኘ።የእኛንም ጉድለት ጌታ ይሙላልን ። ማድጋ የሆነው ሕይወታችን ጣዕም አልባ፣ፍቅር አልባ፣ሰላም አልባ፣በረከት አልባ ሆኗልና ጌታ መድኃኔዓለም ስለ እናቱ ብሎ በመለኮታዊ ጸጋው ያስተካክልልን።
... (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 2) ---------- 1፤ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
2፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
3፤ የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
4፤ ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
5፤ እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
6፤ አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
7፤ ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
8፤ አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
9፤ አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ።
10፤ ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
11፤ ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
See More

User

**ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ሙሽራ ናት**
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። " እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14:33)
... እግዚአብሔር በመንፈስና በእውነት የሚመለከው በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ውስጥ ነው።በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያንን ስንመለከት ፍጹም መንፈሳዊ ጸጋ የተላበሱ፣የእግዚአብሔ� � መንፈስ ረቦ የሚታይባቸው ናቸው።
ቤተክርስቲያኒቱ በፍጹም መንፈሳዊ ውበት ደምቃ፣ሙሽራዋ ክርስቶስን በቅድስና የምታገለግል የሰማይ ደች ነች። ሰማያዊውን ሥርዓት በምድር የምታሳይ፣እንደ ካህናተ ሰማይ የወርቁን ጥና በእጃቸው በያዙ ሽማግሌዎች ለታረደው በግ ውዳሴና አምልኮን የምታቀርብ፣የዓለሙን ቤዛ ክርስቶስ ኢየሱስን ከፍ አድርጋ ለትውልድ የምታሳይ፣በማይናወጽ ዓለት ላይ የተመሰረተች የቅዱሳን ሀገር ነች።
ቤተክርስቲያኒቱ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዋጋ ከፍለው የጽድቅን አክሊል ከተቀዳጁ ቅዱሳን ጋር በመንፈስ አንድ ሆና የምታመልክ ክርስቶስ ራስ በሆነላት በምድራዊቷና በሰማያዊቷ ሕብረት ተጠቅልላ ዙፋኑ ስትባርክ የምትኖር የቅድስና አውድ ናት።
በሀገራችንና በዓለም ዙሪያ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውጪ ያሉ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያለው ልምምድ ስንመለከት ፈጽሞ ከመንፈሳዊ ጸጋ የተራቆተ የሥጋና የደም ፈቃድ የሰለጠነበት ነው።እርኩሳን መናፍስት ትውልዱ ላይ አዚም አድርገው ሲጫወቱበትም እያየን ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ በየአዳራሹ አያስጮኽም፣አያዘልልም� �አይንፈራግጥም፣መሬት ላይ አያንፈራፍርም ። የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ባለበት በዚያ ሰላም፣ፀጥታ፣ተመስጦና መረጋጋት ብቻ ነው ያለው።መጽሐፍ "እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም" ነው ያለው።
ወገኖቼ ወደዚህች ወደ እውነተኛ የአምልኮ ቤታችሁ ተመለሱ።በሰዎች የምላስ ሽንገልና የማደናገሪያ ጥቅስ እየተምታታችሁ ከጽድቅ መገኛ ቤታችሁ ወጥታችሁ አትቅሩ።በቤተክርስቲያ� � ውስጥ የክፋት ልብ ይዘው አመጽና ተንኮልን የሚፈጽሙ ሰዎችን ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ራስ ክርስቶስ ኢየሱስን ብቻ ተመልክታችሁ በእውነትና በመንፈስ እያመለካችሁ ተመላለሱ።
እግዚአብሔር በመቅደሱ እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይትከለን።
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉት።
መ/ር ታሪኩ አበራ
See More

User

**ሁሉም ክርስቲያን ይጠንቀቅ!!!**
**የሐሰተኛይቱ ነቢይት የጥንቆላ ሥራ በእግዚአብሔር ኃይል የፈረሰ ይሁን!!**
«ሐሰተኛይቱ ነቢይት ከምዕራብ አፍሪካ ጠንቋዮች የተዋረሰችውን የመናፍስት አሰራር በይፋ እያወጀች ነው።ተጠንቀቁ!!**
...Contin ue Reading

User

"የአዲስ ኪዳን ታቦት"
The Ark of Covenant in the New Testament
*ታቦት ማክበር ወንጌል አለመረዳት ነውን?*
...Continue Reading

User

**የክርስቶስ ደም ዛሬም ሕያው ነው**
መ/ር ታሪኩ አበራ
የክርስቶስ ደም እንደማንኛውም ሰው ያለ ደም ሳይሆን መለኮት የተዋሐደው ደም ነው።የክርስቶስ ደም አንድ ጊዜ ፈሶ የቀረ ደም ሳይሆን ዛሬም ድረስ ትኩስ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ሕያው ደም ነው።የክርስቶስ ደም ከፈሰሰ ሁለት ሺ ዓመት አለፈው የምንለው በሰው ሰውኛ አቆጣጠር ነው በእግዚአብሔር አቆጣጠር ግን ደሙ ከፈሰሰ ገና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ነው አንድ ሺህ ዓመት በፊቱ እንደ አንዲት ቀን ነች ተብሎ ተጽፏልና፤ ስለዚህም ደሙ ትኩስ ነው።ከተዋሐደው መለኮት የተነሳንም ደሙ ዘለዓለማዊ ነው።መለኮት በባሕርይው ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው።መለኮት የማያረጅና የማያፈጅ ነው።መለኮት የማይሻርና የማይለወጥ ነው።በደሙ በኩል የተገኘው የኃጢአት ሥርየትም ሕያውና ዘለዓለማዊ ነው።
... በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለውን ትውልድ ሁሉ ከበደል ያነጻ፣ ከርኩሰት የቀደሰ፣ እርግማንን ሽሮ የልጅነትን ሥልጣን ያጎናጸፈ የክብር ዘውድ ነው።ይህ ደም ዛሬም በክርስቶስ ቤዛነትና መድኃኒትነት አምኖ ኢየሱስ አዳኜ ነው፣ኢየሱስ መድኃኒቴ ነው፣ኢየሱስ ስለ እኔ ኃጢአት ተላልፎ የተሰጠ ምትኬ፣ ቤዛዬ ነው ብሎ በእምነት ለተቀበለ ሁሉ በደሙ ኃይል ዛሬም ሥርየትና ይቅርታን ሲሰጥ የሚኖር የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።ደሙ ስላለፈው አዳማዊ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዛሬውም መተላለፋችን ወደፊትም ለሚፈጸመው የትውልድ በደል ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ጊዜ የቀረበ ሕያው መስዋዕት ነው።ከክርስቶስ ደም ውጪ እግዚአብሔር ሰውን የሚታረቅበት የጽድቅ መንገድ የለም።ከክርስቶስ ደሙ ውጪ እግዚአብሔር የሚደሰትበት የድኅነት መስዋዕት የለም።ደሙ ዛሬም በኃጢአትና በዲያብሎስ ክፋት ሁሉ ላይ ኃይል አለው። የደሙን ኃይል አልፎ የሚወቅስ ኃጢአት የለም።የደሙን ጉልበት ጥሶም የሚወርድ መዓት የለም። ደሙ ከዲያብሎስ ወቀሳና ከመለኮት ቁጣ የምናመልጥበት ዋስትናችን ነው።
እግዚአብሔር እኛን የሚያየን በልጁ ደም በኩል ነውና ኃጢአታችንን ደሙ ጋርዶታል።እግዚአብሔር የሚሰማው የደሙን ጩኽት ነውና የከሳሽ ጩኽት አድማጭ የለውም።ይህ ደም እግዚአብሔር ዓለሙን የታረቀበት ከመስዋዕቶች ሁሉ የላቀ መስዋዕት ነው።ይህ ደም እንደ ኦሪቱ መስዋዕት በየዓመቱ የሚታደስ ደም አይደለም አንድ ጊዜ ፈሶ ያረጀውን ሲያደስ የሚኖር ደም ነው እንጂ። ይህ ደም እንደ ጠቦቶችና ጊደሮች ደም በሰው ግምባር ላይ የሚረጭ ደም አይደለም በልባችን ላይ ጽላት ላይ ታትሞ የሚኖር ደም ነው እንጂ።
ማንም የበደለ፣በኃጢአትና በነውር የረከሰ ቢኖር በንስሐ ወደ ክርስቶስ ይቅረብ ይቅርታና ምሕረት ይበዛለታል ።ንስሐ ጸጸት ነው።ንስሐ ስላለፈ ኃጢአት ራስን በመውቀስ ዳግም ላለመበደል በቁርጥ ኅሊና ወስኖ በክርስቶስ ፊት ራስን ዝቅ ማድረግ ነው።ከኃጢአት ለመራቅ ከወሰንን በኋላ መልሰን በድፍረት ኃጢአት የወደቅን ከሆነ ግን የደሙን ዋጋ አክፋፍተናልና፣ ዳግም የመስቀሉን ውለታ ንቀን በሌላ በደል ክርስቶስን አሳዝነናልና በቅዱሳን ጸሎት እየታገዝን ዳግም ከውድቀታችን ተነስተን በፊቱ ቆመን ምሕረትን እንጠይቅ ደሙ ሕያው ነውና ሥርየት ይደረግልናል።"የኢየ� �ስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል"1ዮሐ 1፥8 የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ ሊቀበለው የተገባ ነው።
መጽደቂያችን ደሙ ነው።የድኅነታችን ዋስትና ደሙ ነው።ወደ መንግስተ ሰማያት መግቢያ በራችን ደሙ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ደሙ ክብር እንዲህ ብሏል "አኮ ዘንሰውዕ መስዋዕት ካልዐ ከመ ሊቀ ካህናት አላ ኪያሁ ንሰውዕ በጽድቅ" "ዛሬ የምንሰዋው መስዋዕት እንደ ኦሪቱ ሊቀ ካህናት ዓይነት መስዋዕት አይደለም ራሱን የዕለተ አርቡን መስዋዕት ነው።" ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ
"ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው።" ዮሐ 6፥54
አብ ሆይ በልጅህ ደም ልጆችህ አድርገኽናልና ክብር ለአንተ ይሁን።
ወልድ ሆይ በደምህ ወደ ሰማያዊት ቅድስተ ቅዱሳን አስገብተኽናልና አምልኮ ለአንተ ይሁን።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከደሙ ጋር ሕብረትን ፈጥረን ሕይወት ሆነኽናልና ውዳሴ ለአንተ ይሁን።
እባካችሁ ትውልድ የደሙን ዋጋ ይረዳ ዘንድ ለሌሎችም አካፍሉት።/ሼር/
ለበረከት ሁኑ።
See More

User

**እግዚአብሔርን ጠብቁት**
መ/ር ታሪኩ አበራ
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።ከሚደርስብን መከራ ይልቅ የሚደርስልን እግዚአብሔር ታላቅ ነው።የቱንም ያህል በደለኞች ብንሆን ልባችንን ወደ እግዚአብሔር እስከ መለስን ድረስ በፍቅር ተቀብሎ በምህረት የሚጎበኝ አባት አለን።ዙሪያችንን የችግር ገደል ቢከበን ም ቀኛችንን በቀኙ ይዞ ከፈረስ ጭራ በቀጠነች መንገድ ወደ ሰላም ወደብ ሊያሻግረን እግዚአብሔር የታመነ አምላክ ነው።አባታችን እግዚአብሔር በወጀብና በአውሎ ነፋስ መካከል መንገድ ያለው ኃያል ጌታ ነው። ልባችንን ክብሩ ሐሳባችንን ፈቃዱ ይንገስበት።እሱ የእኛ ነውና እኛም የእርሱ ብቻ እንሁን።
... በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጠም፤ማንም በራሱ ፈቃድ ካለመኖር ወደ መኖር አልመጣም።ከመኖር ወደ አለመኖር የሚወስደን አምላክ ለምንኖረው ኑሯችን ኃላፊነት አለበት፣ፈጥሮናልና አይረሳንም።አምጥቶናል� � አይተወነም።ፍቅሩ ግድ ይለዋልና አይጨክንብንም።ጸሎታች� � መልስ ያጣው እግዚአብሔር ሳይሰማን ቀርቶ ሳይሆን በእኛ ላይ ለሚመጣው ክብር በንጽሕና እንድንቀበለው እግዚአብሔር የዝግጅት ጊዜ እየሰጠን ነው።አብዛኞቻችን ግን እራሳችንን ከማየት ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ እናማርራለን።
ወዳጄ ለጸሎት ከቆምክበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ሰምቶሃል፤ጸጋና ረድሄቱ በአንተ ላይ እንዳይፈስ ግን ልብህ ንጹሕ አይደለም ክፋትና ተንኮል ሞልቶታል፣አንደበትህ ንጹሕ አይደለም በሐሜትና በስድብ ቆሽሿል፣እጅህ ንጹሕ አይደለም በደምና በጉቦ፣በጥላቻ ጦማር ጨቅይቷል፣ሰውነትህ ንጹህ አይደለም በዝሙትና በስካር፣በአደንዛዥ ዕፅ ረክሷል።እህቴ ሆይ! ሕይወትሽን አስተካክይ ጸሎትሽ መልስ ያጣው እግዚአብሔር የሚሰጥሽ አጥቶ ሳይሆን የምትቀበይበት ንጹሕ ስፍራ ስለሌለሽ ነው።
የሰው ልጅ ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ ነው፤ባህሩን ስንሻገር በረሀ እየገጠመን እንጨነቃለን።ፈርዖን ወደቀልን ስንል ሳዖል እየተነሳብን እንሸማቀቃልን።ከእግዚ� �ብሔር ጋር እንሁን እንጂ ባህሩም የብስ፣በረሃውም ለምለም ይሆናል።እግዚአብሔርን ጋሻዬነህ ብለን እንነሳ እንጂ ጠላት ዓይኑ ራሳችንን በዘይት ይቀባል።
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው።ኃያላንን ያዋርዳል፣ነገሥታትን ከዙፋናቸው ይሽራል፣ብርቱዎችን አቅም ቢስ ያደርጋል።የተዋረዱትን ያከብራል፣የተናቁትን ይሾማል፣እግዚአብሔር የምስኪኖች ረዳት የደሀ አደግ አባት ነው።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ከእኛ ሥራ ይልቅ የአንድያ ልጁ ሥራ ሚዛን የሚደፋበት፣ከበደላችን ይልቅ የልጁ ጽድቅ በፊቱ የሚታይለት ፣በፊቱ ለወደቁ ስሙን ጠርተው ለተማጸኑ የሚምር ፣የሚራራ፣ስብራትን የሚጠግን ጻድቅ አባት ነው። እግዚአብሔርን በእምነት ጠብቁት ዕንባችሁን ያብሳል፣ማቃችሁን ቀዶ ደስታ ያስታጥቃችኋል፣ክብርን እንደ ሸማ፣ጸጋውንም እንደ መጎናጸፊያ ያጎናጽፋችኋል።
ክብርና ምሥጋና አምልኮና ጌትነት በዙፋኑ ላለው ጌታ ይሁን።
እባካችሁ ለሌሎችም አካፍሉት።/ሼር/
See More

User

እግዚአብሔር በቃሉ ያሳርፈን
ለሌሎችም ሼር አድርጉት

User

***ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው*** ምሳ.22፥6
**እናንተ ከጫካ ብትወጡም ጫካው ግን ከእናንተ አልወጣምና እባካችሁ ነፍሳችሁን በአምልኮ መንፈሳችሁን በዝማሬ ቀይሩት።የሀገር ታሪክ የሚለወጠው በእግዚአብሔር ጣት እንጂ በመሳሪያ አፈሙዝ አይደለም።**
መ/ር ታሪኩ አበራ
...Continue Reading

User

**ዘረኝነት የትውልድ ነቀርሳ ነው**
**የእነዚህን ህጻናት ዕንባ አይቶ ዘረኝነትን የማይጸየፍ ሰው እርሱ ከፈርዖን ወገን ነው**
መ/ር ታሪኩ አበራ
... በዘረኝነት የሚነሳ የእርስበርስ ደም መፋሰስ እና ማፈናቀል በጨቅላዎች ላይ የሚያደርሰው ሰቆቃ እጅግ ልብ የሚሰብር ነው።በሌላው ሀገር ላይ የደረሰው መበታተንና መፈራረስ ለእኛ ትምህርት ሊሆነን ይገባል።እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዘረኝነትን አጥብቆ ይጸየፍ፣ ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር ይኑር፤ አሊያ ግን የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እያንዳንዱ ልጁን በየሜዳው በትኖ ወደ መቃብር ይወርዳል፤ልጆቹም በምድር ላይ ተንከራታችና ተቀብዝባዥ ሆነው ተበትነው ይቀራሉ።
በጣም አጭር ለሆነች ዕድሜያችን እርስበርስ እየተነካከስንና እየተባላን ኋላቀር ሆነን አንቅር።ዘረኝነት ጠባብነትና ኋላቀርነት ነው።ዘረኝነት ትውልድን ደም ሲያቃባ የሚኖር የዲያብሎስ የክፋት ሴራ ነው። ዘረኝነት ምንም የማያውቁ አዲስ ትውልዶችን በክፋትና በጥላቻ መንፈስ እንዲያድጉ የሚመርዝ የአጋንንት እንክርዳድ ነው።
እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ቋንቋ የፈጠረን ልዩነት ውበት ስለሆነ ነው።እንደ ባለ ብዙ ኅብረ ቀለም አበባ የሚያስደንቅ ልዩ ልዩ ተፈጥሯዊ ጸጋ ሰጥቶ የፈጠረንም ተሰጧችንን በደስታ እያጣጣምን የማይሰለች ሕይወትን በምድራችን ላይ እንድንኖር ነው። እኛ ግን በልዩነታችን ውስጥ አንድነትን ፈጥረን ከመኖር ይልቅ የተሰጠንን ውብ ጸጋ ለክፋትና ለጥላቻ አደረግነው።እግዚአብሔ� � ሁላችንንም አንድ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ አድርጎ ቢያስቀምጠን ሕይወት አሰልቺ/Boring/ ትሆንብን ነበር። ልዩ ልዩ ቋንቋ፣ልዩ ልዩ ታሪክ፣ልዩ ልዩ ባህል፣ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ዕሴት ይዘን መኖራችን እጅግ ውቦችና ማራኪዎች አድርጎናል።አንዱን አይተን ስንጨርስ ሌላውን ስንመረምር፣ሕይወት በምድር ላይ ጣፋጭና ደስታ የሞላባት ትሆናለች። ሰይጣን ግን ይህን መልካም ገጽታችንን እየጋረደ በጥላቻ ዓይን እንድንተያይ በማድረገ እያናከሰን ነው።
ወገኔ ሆይ ንቃ! ዛሬ ዓለም ልዩነት ውበት መሆኑ በደንብ ገብቶት ነጩ ከጥቁሩ፣አውሮፓው ከኤዥያው እየተዋሐደና እየተዋለደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሷል።በእውቀት ሰልጥኗል፣በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተራቋል፣እግዚአብሔር የሰጠውን አዕምሮ ለበጎ ሥራ እያዋለ በየቀኑ አዳዲስና ድንቅ ፈጠራዎችን ሲፈጥር ያድራል።እኛ ግን በዘረኝነት መርዝ ተበክለን ቀንና ሌሊት ስለ ማንነት እና ስለ ዘር አጥንት ስንቆጥር ውለን እናድራለን።የእኛ አዕምሮ መቆሸሹ ሳያንሰን በየሶሻል ሚዲያው 24 ሰዓት ስለዘረኝነት እያቀነቀንን የትውልድ አዕምሮ ስናቆሽሽ እንኖራለን እባካችሁ ወገኖቼ ወደ ልባችን እንመለስ።
ክርስቶስ የሁሉ አባት፣የሁሉ እረኛ፣የሁሉ አምላክ ነው እኛም በክርስቶስ የሆንን ሁላችን አንድ ቤተሰብ ፣አንድ ሕብረተሰብ፣አንድ ዜጋ ነን።ቋንቋ አይለያየን፣ወንዝ አይከፋፍለን፣ክልል አይበታትነን።
አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ጉ� �ጌ፣ሲዳማ፣ወላይታ፣አፋ ር፣ቤንሻንጉል፣ሱማሌ ሁሉም ዘር ክርስቶስ የሞተለት፣በክርስቶስ ደም ነጻ የወጣ ለእግዚአብሔር መንግስት የተለየ ሕዝብ ነው። የዘር ትንሽና ትልቅ የለም።አንዱ አንዱን እየተጸየፈ የዲያብሎስ ተባባሪ አይሁን።ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ በመስጠት እስከ መስቀል ሞት ድረስ ከወደደን እኛ እርስበርስ መዋደድና መከባበር ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ነው።
ሌላውን ዘር እየጠላና እየተጸየፈ እኔ ክርስቲያን ነኝ የሚል ማንም እርሱ ውሸታም ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሰው ክርስትና ገና ያልገባው ከጣዖት አምላኪ የማይተናነስ ፍርድ የሚጠብቀው በደለኛ ነው።
" አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 3:28)
ፌስቡክ ላይ ተቀምጣችሁ ስለ ዘረኝነት ስታወሩ የምትውሉ ሰዎች እባካችሁ በክርስቶስ ደም ይሁንባችሁ አቁሙ።የእናንተ አዕምሮ አንድ ጊዜ ተብክሏል ወደ ሌላው ሰው አታስተላልፋ ።አርፋችሁ ቤታችሁ ተቀመጡ።ስላለፈው በደላችሁ ንስሐ ግቡ።
እባካችሁ ሼር በማድረግ ዘረኞችን ከክፋታቸው እንመልስ
See More

User

እግዚአብሄር አምላክ የአገልግሎት ዘመንህ ለዘልአለም ያርዝምልን ። ከክፉ ሁሉ ይጠብቅልን።

User

በጥበብ ያሳደገህ አምላክ ይክበር፡፡ የበለጠ ፀጋና ጥበብ እንዲሰጥህ እንፀልያለን

User

መምህር በጣም አከብርሃለሁ እወድሃለሁ ጌታ ፀጋው ያብዛልህ አይዞህ በርታልኝ ጌታ ከአንተ ጋር ነው

User

መምህራችን እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመንሆን ይባርክ

User

betam grum menfesawi timhirtochinina merejawochin agignichebetalew. mirt page!!!

User

Thank you for sharing the truth 😎🤔, May GOD bless you more memhir 🙏🙏🙏

User

Memir...bemecheresham bebzu dikam pagihi. Agegnew ...ye ewunet yewengelarbegnaneh ...enwedhalen tewhdon ftaryyitebkilin

User

Egzehaber yisxilin

User

መምህር በ እውነት፡ እጅግ ድንቅ ስለሆነው አስተምህሮት፡ነፍስን የሚያለመልም ቃለ ወንጌል ፣በምርጥ ቃላት የተከሸነ ግልፅ አናበቀላሉ የሚገባትምህርት ስለሚያቀርቡልንእዚያአ� �ሔር አገልግሎትዎን ይባርክ ሙሉ ጤና እረጅም፣ እድሜን ያድልልን!! ሁሌም በጉጉት እነብ አለሁ ትልቅ የነፍስ እርካታም እያገኘሁ ፤ለሌሎችም አጋራለሁ !

User

I don't know who I am so I can't give any suggestion about any nature

User

Be blessed brother! Keep on preaching the true Gospel of our Lord and saviour Jesus Christ, like our former fathers, the apostles!

User

Ant Zem blh protestant atbl yegzabhrn hezb sem yemtatfa kewdet edwdqh mjmrya ewq egzabhern fera bemeda edhna edh bemalth teqmh bzu lehon yechelal wesht gn ksetan nw engna gn yemnastmrw (yemnamnw) bab. Bwld. Bemnfs qedus ad amlak becha nw antm bze becha emnena Dan lelochenm aden tmls keteqm yzlalm hywot yeshalal kezh emnt lela aywklenm yhast astmarwoch begzabhr bet tentm nebru wegl watachw ahunm beq lelu bechlu kemtfatna be wegel kemwat lela menm ayamtm wegel (eysus) teshnfo ayweqm bat bet sehtet magneth nw yehm yshenft melkt nw phto eysbesbk protestant atbl ywahoch setsdbun newayachwn bdsta leyafsulachu yechlau yezlalm hiwot gn aynorhm wegne hewot (eysus) yeshalal tmls tmls!!!

User

በመጀመሪያ ፍፁም በሆነው በክርስቶስ ፍቅር እለምንሃለሁ መልእክቴን እንድታነበው እንዳታጠፋው እንደተለመደው

መልካም ብለሀል #መምህር #ታሪኩ #አበራ ነገር ግን አንተ እራስህ ማነህ በጥንታዊቷ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የምትነግድ ተዋህዶ ትታደስ የምትል አይደለህምን??? የነፖስተር በግአሻው ግሩፕ አይደለህምን??? ታዲያ ዛሬ ደርሶ ተቆርቋሪ መሆንህ ለምን ህፃን ክርስቲያኑን ለማወናበድ! ሲጀምር እውነተኛ የተዋህዶ መምህር ከሆንክ ስለምን የተዋህዶን አስተምሮ የማትፅፍ? የኢየሱስን አምላክነት፤ ተማላጅነት ፤ፈራጅነት፣ በቤቱ የተሰገሰጉ ሃሰተኛ የኦርቶዶክስ አባቶችና ፣መምህራን እንድንጠበቅ ብለህ ባስተማርክ ነበር !!!

አንተ ግን ከኛ የተለዩትን ሐሰተኛ ፓስተሮች ማለትህ እውነተኞቹ የምትላቸው የትኞቹን ፓስተሮች ይሆን አሉ ግን? ደግሞስ ስለ ሌላው ቤት ምን አሳሰበህ

በሌላFB አካውንትህ ላይ ለተሀድሶዋ ዘርፌ ከበደ መልስ ይሆን ብለህ ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ሎቱ ስብሐትና በፅሁፍህ ላይ" የኢየሱስ አማላጅነት በኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታን አስተምሮ ብለህ " በፃፍከው ላይ በሰጠሁክ አስተያየት ላይ ወዲያው አጥፍተህ እኔን block አደረግከኝ ልክ እንደኔ፥ስህተትህን የነገሩህ ብዙ የተዋህዶ ልጆችን block አደረግክ! አየህ ለዛ ነው አንተ ማነህ እራስህን ግለጥ የምልህ!! ሳትኖርበት ኦርቶዶክስ ነኝ አይሰራም የተሀድሶ ስልታችሁ በግድ ኦርቶዶክስ ነኝ ነው።በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ዘርፌዋ እንዲሁ ክብር ይግባው፣እና ኢየሱስን አማላጄ ፣እያለች ደግሞ ኦርቶዶክስ ነኝ ብላ ነበር አይን ያወጣ ውሸት! ኦርትቶዶክስ ሳይሆኑ የማያምኑበት መስቀል እና ቀሚስ በመልበስ አማኙን የምታደናግሩ በእውነት በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ናችሁ ዳሩ ቃሉ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው! የበግ ለምድ ለብሰው የሚመጡባችሁ ነጣቂ ተኩላ ተጠበቁ አይደል ቅዱስ ቃሉ ፤ቃሉ መፈፀሙን እኛም አየን፥ተማርንባችሁም፣ መቼም block ካደረግከኝ በድጋሚ አረጋግጣሉሁ ስለማንነትህ ፡ በራስህ ከተማመንክ መልስ መስጠት እንጂ block ማድረግ አላማህ ሌላ መሆኑን ያሳየናል ፡

እናም ፡በክርስቶስ ፍቅር እለምንሀለሁ ወደ ቀደመቸው ሃይማኖት እውነተኛው ንጉሱ ክርስቶስ፣ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ቅዱሳን መላዕክት፣

ፃድቃን ሰማዕታት ወዳሉበት ወደ ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህብረት ተመለስ ነው መልዕክቴ ። አስተዋይ ልቦና እግዚአብሔር ያድልልን ።

User

Mamher tariku:-GETA EYASUS eko WANGELEN wade alem heduna sebaku ale enjy WONDMEKEN behasat ena alubalta kisas(wanjel) ALÀLEM ! (Ye Ģhanaw teret teret Egzeabher aywadewm lelam lelam ale. EYASUS GETA NAWE!!!

More about መምህር ታሪኩ አበራ/Emmanuel International Gospel Ministry Based On Eotc

መምህር ታሪኩ አበራ/Emmanuel International Gospel Ministry Based On Eotc is located at Sw16 2DH London, United Kingdom