ኢትዩ ላቭ/Ethiopian Love

About ኢትዩ ላቭ/Ethiopian Love

ለሰው ልጅ ሁሌም መልካሙን ነገር እንመኝ። መልካምነት ለራስ ነውና መልካም ለመሆን እንጣር ።

ኢትዩ ላቭ/Ethiopian Love Description

It also touches all

Reviews

User

እሾህና አሜኬላ የበዛበት አገር መሪ ሁኖ ነው እንጅ እውነት ለመናገር ከልብ ሰብዕናን የተላበሰ መሪ ነው እሄን ሰው አለማድነቅ በእውነት መረገምና አለመታደል ነው.👌💝👌💝👌💝👌ይሄ ነው ኢትዬጲያዊነት 💚💛❤️👏👏👏

User

የአሸናፊ ሰዎች የህይወት ህጎች
ሚካኤል ሊትፋክ የተሰኘ ዝነኛ የሳይካትሪ ባለሙያ በህይወታችን አሸናፊ ለመሆን የግድ ያላቸውን 12 ህጎችን ጠቁሟል፡፡ እኔም ተርጉሜ አካፈልኳችሁ፡፡ ቢያንስ ለአንድ ሰው የሚጠቅም ከሆነ እርስዎ ደግሞ ለሌላ ሰው በማጋራት እንደሚረዱኝ እያመንኩ ቀድሜ አመሰግናለሁ፡፡
1. መራቅ - ስለ ህይወታቸው እንድስ እንኳ በጎ ነገር ከማይወጣቸው ሰዎች ራስህን አርቅ፡፡ ስለሌሎች አንዳች ነገር የማይረባ ሊያወሩ እንደሚችሉም አስብ፡፡
... 2.መጥለቅ- በአንድ ነገር ጥልቅ ማለት ከፈለክ በሳይንስ እና በእውቀት ምንጮች መጥለቅን ልመድ፤በሌላ ሰው ግላዊ ህይወት ጥልቅ ከማለት ይልቅ፡፡
3.ጭንቀት- የመደበት (የመጨነቅ) ስሜት ካለብህ እራስህን እንደገና መርምር፡፡ የመጨነቅ ምልክት ወደ ውስጥ ማየት መርሳትህን ለማስታወስ ሊሆን ስለሚችል፡፡ ስለዚህ ወደ ውስጥህ መጥለቂያ ጊዜ ይኑርህ፡፡
4.የደስታ ምንጭ ‑ራስህ ለራስህ ፍቅር ስጠው፡፡ ደስታ ዝራ ደስታ ኮትኩት፡፡ ለመደሰት የሌሎች ሰዎችን አረጋጋጭነት አትሻ፡፡
5.አሁኑኑ- ማድረግ የምትሻውን ነገር አሁኑኑ አድርግ፡፡ ማከናውን ያለብህን ነገር አሁኑኑ ከማከናወን ይልቅ የሌሎች ሰዎችን አረጋጋጭነት (ፈቃድ) ስትሻ አትዘግይ፡፡ ፈቃዳቸውን ላይቸሩህም እኮ ይችላሉ፡፡
6.ያወቅከውን ተግብር- ያልበሰሉም ሆነ ብልህ ሰዎች እውቀትን ያከማቻሉ፡፡ በማከማቸት ቢመሳሰሉም ብልህ ሰው ግን ወዲያውኑ እውቀቱን ይጠቀምበታል፡፡ ብልህ ያልሆኑ ሰዎች ያገኙትን እውቀት እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ስለማያውቁ ሲተቹ ይኖራሉ፡፡
7.ተቀባይነት- የሁሉንም ሰው ተቀባይነት ለማግኘት መፈለግ የመወድቅ አጭሩ መንገድ ነው፡፡ የምትሰራው ስራ ሌሎች ሰዎችን እንደማይጎዳ እርግጠኛ ከሆንክ ሌሎች ሰዎች እንዴት ነው የሚስሉኝ ለሚለው አትጨነቅ፡፡
8.ስኬት-የጀመርከውን ራስ መር የስኬት ጉዞ የሌሎች ሰዎችን አፅዳቂነት በመጠበቅ እንዳታቋርጥ፡፡ የሚሰነዝርብህ ትችትም ሆነ ነቀፌታ ስኬታማነትህ ሲጨምር እየቀነሰ እና እየተነነ ይሄዳልና፡፡
9. የተጋነነ የራስ ክብር እና ግንኙነት- የንግድ ም ሆነ የጋብቻ አጋርነት የማቋረጥ እርምጃ እራስህን የሚያበለፅግህ ካለሆነ በቀር ፈጽሞ አትሞክረው፡፡ በንግድም ሆነ በፍቅር ግንኙነት የተጋነነ የራስ ክብር ጠልፎ እንዳጥልህ ተጠንቀቅ፡፡
10. ደሰታ- ደስታን አታሳድድ፡፡ ደስታ ባልጠበከው ቦታ ሊገኝ ይችላል፡፡ በራስ እድገት ላይ የሚገኝ ደስታ ዘላቂ ስለሆነ እሱኑ አሳድድ፡፡
11. ህልም እና ችሎታ- የምታልመውን ነገር በችሎታ አስደግፈው፡፡ የማታገኘውን እና የማትሞክረውን መመኘት ብቻውን የቀን ህልም ነው፡፡ ስለዚህ ወይ ችሎታህን ወደ ህልምህ ሳበው አለያ ደግሞ ህልምህን ወደ ችሎታህ አውርደው፡፡
12. ከሰው እና ከመፅሀፍ- ሰዓትህን ከሰዎች ጋር ወይንም ከመፅሀፍት ጋር ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡ ባዶ ጭንቅላት ካለው ሰው ጋር ጊዜ ከመግደል ይልቅ ቆንጆ መፅሀፍ ጋር ጊዜ ማሳለፍን ምረጥ፡፡ ቆንጆ መፅሀፍ ጋር በማሳለፍ የሆነ ነገር ማግኘት የማይቀር ሲሆን ከማይረባ ሰው ጋር ማሳለፍ ግን ሰዓትን መግደል ነው::
See More

User

አድዋ የፊታን የካቲት መከበሩን አስመልክቶ እስቲ ስለ ጀግኖች አባቶቻችን ካነበብኩት ላካፋላችሁ.... የአምባላጌው ጀግና የጦር አበጋዙ ፊታውራሪ ገበየሁ (አባ ጎራው)!!! የንጉሰ ነገስቱ የመሀል ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረገው በሁሉም ጦርነት የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ፡፡ የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር በጣሊያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደውል ያሰሙት እና ዋናው የድሉ ባለቤት እሳቸው ነበሩ፡፡በዚህም ምክንያት በወቅቱ የፈረንሳይ ጋዜጦች “የአምባላጌው የኢትዮጵያ ጀግና” በማለት እንዳወደሷቸው ተክለፃዲቅ መኩሪያ ፅፈዋል፡፡ የመቀሌውንም ጦርነት በደንብ ተካፍለው በጀግንነት ሲዋጉ እጃቸውን የቆሰሉ ሲሆን ፣ ከጦርነቱ በፊትም ራስ መኮንን ስለ እርቅ ጉዳይ በሚነጋገሩበት ጊዜ ገበየሁ እየተዋጉ ስላስቸገሩ እንደ አምባላጌው እንዳይዋጉ አስረዋ...ቸው ሳለ በኋላ ግን ላይዋጉ አስምለው አስለቀቋቸው፡፡ በኋላም ጦርነቱ ሲጀመር የአምባላጌ የገፈቱ ድል ቀማሽ ፊታውራሪ ገበየሁ አባ ጎራ ነበር። በእለቱ ታሞ ስለነበር ዱላ እየተመረኮዘ ነበር ገደሉን የወጣው፤ ግና ይህ ሁኔታው ድልን ከመቀዳጀት አልከለከለውም። ስሙን ትንሹም ትልቁም ወዲያው አወቀው እና ገጣሚም እንዲህ ሲል አሞገሰው፦ የንጉሥ ፊታውራሪ ያ ጎራው ገበየሁ አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው ለምሳም ሳይደርሱ ቁርሥ አደረጋቸው ተብሎ ተገጠመለት፡፡ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ የአድዋ ድል ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በጦርነቱ ላይ የተሳተፉ ጀግኖች ኢትዮጵያውያንም እንዲሁ፡፡ የአደዋ ጦርነት የተጀመረው በየካቲት 23 ቀን 1888ዓ.ም ከማለዳው ነበር፡፡ ውጊያው ከጠዋቱ 11፡30 ላይ በአራት ጄኔራሎች የሚመራው የጠላት ጦር በፊታውራሪ ገበየሁ ፣ በዋግሹም ጓንጉል ፣ በራስ ሚካኤል እና በራስ መንገሻ ጦር ላይ በሰነዘረው ጥቃት ተከፈተ፡፡ፊታውራሪ ገበየሁ በዚህ ጦርነት ፊት ለፊት የገጠሙት በእንዳ ኪዳነ ምህረት በኩል የመጣውን እና በጄኔራል አልበርቶኒ የሚመራውን የጠላት ጦር ነበር፡፡በጦርነቱ ፊታውራሪ ገበየሁ ከሰራዊቶቻቸው በመለየት ጎራዴያቸውን መዘው በዋናው የትግል አውድማ ፣ በተፋፋመ እና በቀለጠው ውጊያ ላይ ተወርውረው ገቡ፡፡ ዘለው እንደገቡም ከጀግናው ጓደኛቸው ከቀኝ አዝማች ታፈሰ ጋር እየፎከሩ የጠላትን አንገት በጎራዴ ሲቆርጡ እና ሲገነድሱ ቆይተው ከርቀት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ወደቁ፡፡ ሌሎችም አዝማቾች እና መኮንኖች እንዲሁም ተራ ተዋጊዎች ሞተዋል፡፡ በጊዜውም እንዲህ ተገጠመ፡- ያ ጎራው ገበየሁ ምን አሉ ምን አሉ ያ ትንታግ ታፈሰ ምን አሉ ምን አሉ እነ ደጃች ጫጫ ምን አሉ ምን አሉ ተማምለው ነበር ከጦሩ ሲገቡ አገሩን አቅንተው አደዋ ላይ ቀሩ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ ፊታውራሪ ገበየሁ አዲስ አበባ ድረስ ተማርኮ መጥቶ የነበረው የኢጣልያ መኰንን ፣ጆቫኒ ቴዶኒ የጻፈው ማስታወሻ እንዲህ ይላል….. “በቢያን ኪኒና በማዘቶ ለሚመሩት መድፎች እየተመቱ አበሾች ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ አይቶ “ፈሪ አንዴት ትሸሻላችሁ እኔ እንዴት እንደምሞት ለንጉሱ ሄዳችሁ ንገሩ” በማለት ፈረሱን በአለንጋ አስነስቶ በግልቢያ በሚዘንበው የመድፍ ጥይት መካከል ገባ፡፡እሱን ሲያይ ሁሉም እየሮጠ ተከታትሎ ገብቶ ከመድፈኞቹ ጋር ተጨፋጭፎና ገድሎ መድፈኞችን ማረከ፡፡ የገበየሁ ሬሳ ከወደቀበት ቦታ የእኛዎቹ ጀግኖች አብረው በመውደቅ የእርሱን ሬሳ አከበሩት” በማለት ገልጾታል፡፡እነዚህ ጀግኖች አይረሴ የአድዋ ጌጥ እና የጥቁር ህዝቦች ሰማዕት ናቸው፡፡ ፊታውራሪ ገበየሁ ገና ወደ አድዋ ሲዘምቱ ተናዘውም ነበር “ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፣ እኔ እንደ አባቶቼ አይደለሁምና ወግ አይገባኝም፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን እሬሳዬን /አፅሜን/ ትውልድ ቦታዬ ውሰዱልኝ” አሉ ::
See More

User

የሪህ በሽታ መንስኤዎች/ Gout ***********
ሪህ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲሆን ሰውነታችን ለማስወገድ አቅም ያጣል፡፡ በዚህን ጊዜ ካልሼም ፎስፊት ወደሚባል ጠጣር ንጥረ ነገርነት ተቀይረው ወደ መገጣጠሚያ ቦታዎች ይሰበሰባሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የተከማቸው ዩሪክ አሲድ በኩላሊት ውስጥ እና በሽንት ማመላለሻ መስመሮች ውስጥ በመዝቀጥ የኩላሊት ጠጠር ሊፈጥር ይችላል ፡፡
...  ለሪህ የጤና ችግር በመንስኤነት የሚገለፁ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡ – የዕድሜ መጨመር – በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ የንጥረ ነገሮች መፈጠርና መከማቸት – በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አማካኝ /infection/ – ከቤተሰብ መካከል የጤና ችግሩ ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድል ይኖረዋል – ምክንያታቸው በውል የማይታወቅ ጉዳዮች /idiopathic/
 ተጋላጭነተወዎን የሚጨምሩ ነገሮች
ለሪህ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ቀይ ሥጋ፣ ጉበት ኩላሊትና የጭንቅላት ስጋን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ለሪህ በሽታ ተጋላጭ የመሆን ዕድልን ያሰፋሉ፡፡ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ - የሰውነት ክብደት መጨመር፣ - በቁጥጥር ስር ያልዋለ ደም ግፊት፣ - ውሃ በብዛት ያለመጠጣት፣ - የኩላሊት በሽታና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለሪህ በሽታ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡  የህመሙ ምልክቶች -ከትንሽ የጣት ጫፍ እስከ ትላልቆቹ የሰውነት ክፍሎች አካባቢያሉ መገጣጠሚያ ቦታዎች ያብጣሉ – የሰውነት ትኩሳት መከሰት – ከቁርጥማት ጀምሮ መላ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በመንካት እስከሚቸግር ድረስ ህመም – ከፍተኛ ስቃይ ያለው ህመም – መገጣጠሚያ አካባቢዎች በተለይ መልኩ መቅላት – በመገጣጠሚያ አካባቢዎች የማቃጠል ሁኔታ ይከሰታል – የጡንቻ መዛል በተለይ ጠዋት ጠዋት እጅና እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር ይኖራል – የጤና ችግሩ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ በመገጣጠሚያ ቦታዎች ጠጣርየሆኑ ነገሮች ይፈጠራሉ – በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ – ቁርጥማት – በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡
 ህክምና
አንድ ሰው ለመጀመሪያ ወይም በተደጋጋሚ ጊዜ የሪህ በሽታ ከተከሰተበት ከፍተኛ ስቃይ ይኖረዋል፡፡ የመጀመሪያው የህክምና ስቃዩን ለማስታገስ የሚያስችል መድሃኒቶች ይታዘዛሉ ፡፡ በዚህ ረገድ Non-Steroid Anti-Inflamaty drugs /Nsaids/ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለውጥ ካልመጣ Corticoid Steroids የሚባሉ መድሃኒቶችን በመርፌ ወይም በሚዋጥ መልክ ይሰጣል ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የህመም ስቃይን ከማቃለል በተጨማሪ መገጣጠሚያ ከጥቅም ውጭ እንዳይሆን ለጊዜው ፋታ ይሰጣሉ፡፡
ሌላኛው የህክምና ዘዴ Uric acid ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ የሚችሉ መድሃኒቶች ነው፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡ እጅና እግር መንቀሳቀስ ካቆመ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡
---
source - helath insurance network
See More

User

በእውነት ትልቅ ትምህርት ነው ተመስገን አምላኬ! ደጋግመው ደጋግመው ቢሰሙት የማይሰለች

User

ውብ የኢትዮጲያ ልጆች ባሕላችሁን አዋቂ እስካለባበሳችሁ በጣም ደስ ይላል።

User

"<ምን ይሰማቸው ይሆን>" ይህን ነገር ለጋሼ ምን ብለን ይሆን የምናስረዳቸው እንዴትስ ብለን ይሆን የምንገልጥላቸው?እሳቸው� �� እንዴት ብለው ነው የሚያምኑን?ይህን ሁሉ ነገር ቁጭ ብሎ የሚያስረዳቸውስ ማነው?
ጋሼ(ሼክ መሀሙድ አላሙዲን) ተፈተው ከሳውዲ አዲስ አበባ ሲገቡ :... ሀይለማሪያም ወርዶ አብይ ተተክቶ : መስቀል አደባባይ ተጥለቅልቆ ቦንብ ተጠምዶ : ጀዋር ከሚኒሶታ አዲስ አበባ ከትሞ : ታማኝ አዲስ አበባ ገብቶ ጎንደር ሂዶ ዲሲ ተመልሶ : አንዳርጋቸው ተፈቶ ብርሀኑ ነጋ አዲስ አበባ ገብቶ : ፕ/ሮ መራራ ኦቦ በቀለ ተፈተው ፓርቲያቸውን ተቀላቅለው : (አብን)የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ተቋቁሞ የቤቲ ኢንተርቪው አነጋግሮን : እስር ቤቱ ባዶ እንዳይሆን እስር በአብዲ ኢሌ ተጀምሮ : ኦነግ ከነትጥቁ ኢትዮጲያ ገብቶ ቄሮን ተቀላቅሎ : ኢሳት ቲቪ ቢሮውን አዲስ አበባ ላይ ከፍቶ : ቴዲ አፍሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ያስተሰርያልን ዘፍኖ : የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር ተፈተው በአንድ ላይ ቆመው : ልደቱ ፓርቲውን በትኖ ከፖለቲካ ወጥቶ : ዶ/ር አብይ በአሜሪካ አስገራሚ ንግግር አድርገው ተቃዋሚ ጠፍቶ : ኢንጅነር ስመኘው መስቀል አደባባይ ተገለው ተቀብረው : ሁለቱ ሲኖዶስ ታርቀው ስደተኛው ሲኖዶስ ሀገሩ ገብቶ : በረከት ከስልጣን ወርዶ ጌታቸው አሰፋ መንፈስ ሆኖብን : ከቀበሌ እስከ ወረዳ ከወረዳ እስከ ሚንስተር ያልነበረ ኖሮ የኖረ ወርዶ : ኢሳያስ አዲስ አበባ መጥቶ ኢምባሲ ከፍቶ ኢሱ ኢሱ ተብሎ ተዘምሮለት : ኤርትራ ከኢትዮጲያ ታርቃ በአስመራ ኢምባሲ ከፍታ : ፕሬዘዳንት ሙላቱ ወርደው ሳህለወርቅ ተሰይመው : መከላከያ ሚንስተር በሴት ተተክቶ ሳሞራ ጡረታ ወጥቶ : የአዲስ አበባ ከንቲባ ተቀያየሮ አርከበም ጃፓን ሂዶ ተሸልሞ : ሜቴክ ተበታትኖ ባለስልጣናቱ ሼቤ ገብተው : ቢጫ ሂሊኮፕተር ተፈጥራ በሰማይ ላይ በበረች ቁጥር ሁሉ ተሸማቆ : ብቻ ምን ያልሆነው አለ ስንቱን አንስተን ስንቱን እንዘርዝረው እና ይሄን ሁሉ ሼኩ በምን አቅማቸው ነው ሰምተው አምነው የሚቀበሉን ይህ እኮ በራሱ ፊልም የመሰለ ነገር ነው እናም ገና ብዙ ጉድ ይሰማሉ!! እኛም እድሜ ይሰጠን እንጂ ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን።
See More

User

~ ይሄን ሁሉ ነገር ከመቼው ነው እያደረገ ያለው? እረፍት የለውም ወይ እያላችሁ ለምትጨነቁት ሰዎች ሰውየው፦ ውስኪ ቤት አያመሽም በርጫ ቤት አይውልም ሺሻ ቤት እግሩን ሰቅሎ አያጨስም... ፌስቡክ ላይ እየተሰዳደበ አይውልም አንተ ያበላሸኸውን ለማስተካከል እንደ አቦ ሸማኔ ይሮጣል!! ባርነትን ድህነትን የፍትህ እጦትን ጥላቻን ከሀገሬ ለመንቀል እየሮጠ ነው። ጀርመን ፓርላማ መከላከያ ሜቄዶንያ . . . አይደክመውም ይሄ ፎቶ የአዕምሮ ህሙማንን እየጎበኘ ያለበትን ሁኔታ ያሳያል! ይሄንን ሰው እንድትደግፈው ቤትህ መጥቶ ድስትህን ማጠብ አለበት? ታክሲህ ተራ ሄዶ ወያላ ሆኖ ሰው ይሙላልህ? ሱቅህ መጥቶ ንግድ ይቸርችርልህ? መኪናህን ይጠበው? ፖስትህ ስር ኮሜንት የተደረገውን ሰንፈህ ዝም ያልከውን የጓደኞችህን ኮሜንት በአንተ ስም ላይክ ያድርግልህ? እርሻህን ይረስ? ኩበት ይጠፍጥፍልህ? ቡና ያፍላልህ?? . . . . የዘረኝነት ቆሻሻ ከሌለብህ ይሄንን #እንቁ ሰው ለማክበርና ለመደገፍ 95% በቂ ምክንያት በቂ ለውጥ በቂ ተስፋ አለህ!!
እኔና ደጋፊዎቹ ረዥም እድሜ መልካም ጤንነት ሰላም እንመኝለታለን!! ለዶክተር አብይ ጤና መመኘት ለኢትዮጵያ ጤና መመኘት ነው።
See More

User

#" ኢትዮጵያ ደክሟት ይሆናል ግን አልተሸነፈችም። # ሀገሬ ቀጥና ይሆናል ግን አልተበጠሰችም። # እምዬ ታማ ይሆናል ግን አልሞተችም። "ኢትዮጵያ የራሷ ጠባቂ ያላት ታላቅ ሀገር ነች፡፡" ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

More about ኢትዩ ላቭ/Ethiopian Love

ኢትዩ ላቭ/Ethiopian Love is located at Ruby street, London, United Kingdom
07488434188
http://www.ethiolove.com